የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ከንቱ ድካም በአሜሪካ
የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ልዑካን ወደ ሰሜን አሜሪካ ተጉዘው ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያንን የማነጋገር ከንቱ ልፋት ይመለከታል ይህ መግለጫ። የምክክር ኮሚሽኑ በዐዋጅ ቁጥር 1265/24 ሲቋቋም፣ ራዕዩ “እጅግ መሠረታዊ በሆኑ ጉዳዮች ላይ ሀገራዊ መግባባት ተፈጥሮ ማየት” ነው ብሎ ነበር።እሴቶቹን ሲዘረዝር ደግሞ፣ “አካታችና አሳታፊነት፣ገለልተኛነት፣ግልጽነትና ተጠያቂነት፣ብቃትና ሙያተኝነት፣አጋርነትና ትብብር፣ የሕግ የበለይነት፣ ተዓማኒነትና ቅቡልነት” ናቸው ብሎ ነበር። ..........